Learn the numbers in Geez.
ጠያቂ፨ እፎ ወሓልከ እኁየ?
(እንዴት ዋልክ ወንድሜ)
መያጢ፨ እግዚአብሔር ይሰባሕ ኦ እኁየ (እግዚአብሔር ይመስገን ወንድሜ ሆይ)
ጠያቂ፨ መኑ ውእቱ ስምከ?
(ስምህ ማን ነው?)
መያጢ፨ ግሩም እትበሃል፡፡
(ግሩም እባላለሁ፡፡)
ጠያቂ፨ ማዕዜ ተወለድከ?
(መቼ ተወለድክ?)
መያጢ፨ በ ፲፱፻፹ወ፱ ዓ.ም ተወለድኩ፡፡
(በ 1989 ዓ.ም ተወለድኩ፡፡)
ጠያቂ፨ እስፍንቱ አኃው ሀለውከ?
(ስንት ወንድሞች አለህ?)
መያጢ፨ ክልዔቱ አኃው ሀለውኔ፡፡
(ሁለት ወንድሞች አሉኝ፡፡)
ጠያቂ፨ እስፍንቱ አኃት ሀለውከ?
(ስንት እኅት አለህ?)
መያጢ፨ አልብየ እኅት
(እህት የለኝም)
ጠያቂ፨ አይቴ ውእቱ ሀገርከ?
(ሀገርህ የትነው?)
መያጢ፨ ኢትዮጵያ ይእቲ ሀገርየ
(ኢትዮጵያ ናት ሀገሬ)
ጠያቂ፨ አይቴ ውእቱ ተወለድከ?
( የትነው የተወለድከው?)
መያጢ፨ ዐዲስ ጽጌ ውእቱ
(አዲስ አበባ ነው፡፡)
ጠያቂ፨ ለምንት መጻእከ ዝየ?
(እዚህ ለምን መጣህ?)
መያጢ፨ ለተምህሮ ግእዝ መጻእኩ
( ግእዝ ለመማር መጣሁ)
ጠያቂ፨ ሠናይ ትምህርት ይኩን ለከ፡፡
መያጢ-አሜን ጥቀ እሴብሐከ
(አሜን በጣም አመሰግናለሁ)